በአዳማ ከተማ በከተማ መሬት ሊዝ ሲስተም ላይ ስልጠና ተሰጠ


በስልጠናው የማጠቃለያ መርሃግብር የተከናወነ ሲሆን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ከከተማ አስተዳደሩ የተጠሩ አመራር እንግዶች የታደሙበት ውይይት እና የቀጣይ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡ ሲስተሙ በጣም ጠቃሚ የመሬት አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የዲጂታል መረጃ አያያዝን በማዘመን ዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል እንደሆነ ተነስቷል፡፡ በመጨረሻም ማጠቃለያውን ያደረገው ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ ባለሙያዎች ከአመራሮች እጅ የምስክር ወረቀት የመስጠት መርሃግብር ተከናውኖ እንዲጠናቀቅ ተደርጓል፡፡
