ገቢ ለማሳደግ የሚረዱ የጥናት ሰነዶች ላይ ስልጠና ተሰጠ


የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከጅማ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃቤት ጋር በመተባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ *ነሀሴ 21/2018 ጅማ ከተማ* የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከጅማ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃቤት ጋር በመተባበር ከአጋሮ ከተማ እና ከጅማ ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ የማዘጋጃቤት፣ መሬት እና ገቢዎች ቢሮ አመራርና ባለሙያዎች የከተሞችን ገቢ ለማሳደግ የሚረዱ ስራዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በስልጠና መርሀ ግብሩ መክፈቻ ላይ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ተወካይ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ፈለቀ ስልጠናው በሁለቱ ከተሞች የማዘጋጃቤታዊ ገቢን ለማሳደግ እንደሚረዳ በመግለጽ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ባስጠናቸው ጥናቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸው ስልጠናውን በይፋ አስጀምረዋል። በመድረኩ ላይ ከከተሞች ፋይናንስ ስትራቴጂ ሰነድ ጀምሮ የተለያዩ ጥናቶች እና ሞዴል መመሪያዎች በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አመራርና ባለሙያዎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል።